Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በቀጣይ ዓመት በ70 የትምህርት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ዓመት በ70 የትምህርት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደርና መሠረተ-ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብረሃ ከሚመጣው ዓመት ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በ70 ፕሮግራሞች መሰጠት እንደሚጀምር ገልፀዋል።

ስራ አስፈፃሚው ይህን የተናገሩት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2014 ዓ.ም በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015ዓ.ም በጀት አመት እቅድ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

በጦርነቱ የወደሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉ በ2014 በጀት ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ርብርብና ጠንካራ ትብብር የታየበት መሆኑ ተገልጿል።

በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ና በጦርነቱ ምክንያት የወጡ ተማሪዎችን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ በመስጠት ትምህርታቸውን የማስቀጠል ስራ ውጤታማ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ዓለም አቀፈዊ አጋርነት እየጎለበተ መምጣቱ ለቀጣይ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ስኬት በምቹ ሁኔታነት ተገምግሟል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኦዲት ግኝቶችን ለመቀነስ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም የግዥ ሥርዓት መመሪያዎችን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተጨባጭ ሁኔታና ባህሪያት በተለይም ከተማሪዎች አገልግሎትና ምርምር ሥራዎች አንጻር መልሰው እንዲቃኙት ተጠቁሟል ፡፡

በቀጣይ ዓመት በ70 የትምህርት ፕሮግራሞች ለሚሰጠው የመውጫ ምዘና ከወዲሁ ዝግጅት እንደሚደረግ መገለጹንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.