Fana: At a Speed of Life!

“አዋቂ” የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ጊዜውን የዋጁና ወጣቶችን ወደበጎ ነገር የሚመሩ አቀራረቦችን ይዞ መጥቷል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)“አዋቂ” የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ጊዜውን የዋጁ እና ወጣቶችን ወደበጎ ነገር የሚመሩ አቀራረቦችን ይዞ መጥቷል ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡
 
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ÷ በፈርስት ኮንሰልት የተተገበረው “ አዋቂ” የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ በይፋ ተመርቋል፡፡
 
በሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ ወጣቶች በተሰራላቸው ላይ መኖር ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
 
ለዚህም “ አዋቂ” ወጣቶችን በወጣት ቋንቋ ማናገር የሚችሉ ፣ ጊዜውን የዋጁ አቀራረቦችና ወጣቶችን በአስተሳሰብ የሚለውጡ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን ይዞ የመጣ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
 
ለዚህም “ አዋቂ” ወጣቶችን በወጣት ቋንቋ ማናገር የሚችሉ ፣ ጊዜውን የዋጁ አቀራረቦችና ወጣቶችን በአስተሳሰብ የሚለውጡ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን ይዞ የመጣ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
 
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከግል ሴክተሩ ጋር መሥራቱ ለሀገር ግንባታ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን በመጠቆም÷“አዋቂ” የተሰኘውን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከፈጠረው ፈርስት ኮንሰልት ጋር ያደረገው ስምምነትም ወጣቶችን በበጎ ጎዳና በመምራትና የሥራ ዕድሎችን የሚመለከቱበትን ዕይታ ከማስፋት አንፃር ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
 
የፈርስት ኮንሰልት ስራአስኪያጅ አቶ ነቢል ኬሎ በበኩላቸው ፥ “አዋቂ” ከ 17 ዓመት በፊት የተፈጠረ ሃሳብና ለወጣቶች ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የማህበራዊ ሚዲያ ሥራው የግሉን ዘርፍ ወደሥራ የሚያመጣ በተለይ ወጣቶችን ለሥራ እንዲነሳሱ የተፈጠረ ጅምር በመሆኑ የወጣቶችን ክህሎት በማዳበር በኩል በጎ ሃሳቦቻቸውን የሚያጎለብት በመሆኑ ሁሉም ሊተባበር እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
 
የ“አዋቂ “ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወጣቶችን ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን ሥራ እንዲያገኙና ሥራ እንዲፈጥሩ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፥ በ 9 ወር ውስጥ ከ230 በላይ ተከታዮችን ማፍራት እንደቻለ በሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
 
በአንድ ዓመት ውስጥም ከ500 ሺህ በላይ ወጣቶች እንዲከተሉትና ተሰጥኦን መሠረት ያደረጉ በጎ አስተሳሰቦችን በማስረጽ ወጣቶችን ለሥራ ንቁ ለማድረግ እንደሚሰራ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.