Fana: At a Speed of Life!

በምሥራቅ ሸዋ ዞን በተካሄደ የሕግ ማስከበር ዘመቻ 129 የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በአራት ወረዳዎች ላይ በተካሄደ ሕግ የማስከበር ዘመቻ 129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ የተወሰደ መሆኑ ተገለጸ፡፡
 
የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በፀረ ሰላም ቡድኖች ላይ እያካሄዱት ባለው ዘመቻ እርምጃ ከተወሰደባቸው በተጨማሪ ፥ 17 የሽብር ቡድኑ አባላት በሰላም እጃቸውን መስጠታቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከዚህም በተጨማሪም 29 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣10 ሽጉጥ፣ 200 የብሬን ጥይት፣600 የክላሽንኮቭ ጥይት፣ 2 ቦምብ ፣ 56 ሞተር ሳይክል እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.