Fana: At a Speed of Life!

በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገኑ 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ማጣሪያ ውድድሮች በወንዶች 3,000 ሜትር መሠናክል እና በሴቶች የ1,500 ሜትር ውድድሮች ስድስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል።

3,000 ሜትር መሠናክል ወንዶች፣ ጌትነት ዋለ 8:17.49፣ ለሜቻ ግርማ 8:19.64 እና ኃ/ማርያም አማረ 8:18.34 አጠናቀዋል።

በሴቶች 1,500 ሜትር፥ ሂሩት መሸሻ 4:07.05፣ ፍረወይኒ ኃይሉ 4:04.85 እና
ጉዳፍ ፀጋይ 4:02.68 በመሆን አጠናቀው ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.