Fana: At a Speed of Life!

አልማ ከህዝብ በሚሰበስበው ገቢ ከ1 ሺህ 300 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወንኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማህበር ከህዝብ በሚሰበስበው ገቢ በክልሉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ማህበሩ ከ2012 እስከ 2014 ዓመት ከ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዮ ፕሮጀክቶች መስራቱን ገልጿል።

የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፋንታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፥ ማህበሩ ከህዝብ በሚሰበስበው ገቢ በክልሉ ከ1ሺህ 300 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ነው።

90 በመቶ የሚሆነው ስራም ትምህርት ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ በክልሉ በዘንድሮው ዓመት ከ670 በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እየተመረቁ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበሩ አሁንም የሁለት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን በመንደፍ ተጨማሪ ስራዎችን ለመስራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አቶ መላኩ አክለውም ፥ ማህበሩ ባለፉት ዓመታት ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ የጤና ተግባራት ላይ ሰፊ ስራ ሰርቷል ብለዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.