Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ ሽብርተኞችን ድል አድርጎ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ገንብቷል – ሜ/ጀኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠራዊቱ ሽብርተኞችን ድል አድርጎ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ገንብቷል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ ገለጹ፡፡

ምክትል አዛዡ ሠራዊቱ ዛሬም እንደቀደመው ሁሉ የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ መምታት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት አለው ብለዋል፡፡

የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ሊቃጡ የሚችሉትን ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ መክቶ ድባቅ መምታት የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት አለውም ያሉት ሜጄር ጀኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ።

አያይዘውም ሰራዊቱ በስነ-ልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በቴክኒክ ያለውን አቅም ከምንጊዜውም በላይ እያሳደገ መምጣቱን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅትም ሽብርተኛው ህወሓትንም ሆነ ሌሎች ተላላኪ ሽብርተኞችን ድል አድርጎ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ገንብቶ ይገኛል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሠራዊቱ ከመንግስትና ከህዝብ ሊሰጠው የሚችልን ማንኛውንም አይነት ተልዕኮ ተቀብሎ በማንኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ከመላው ህዝብ ጋር በመተባበር ድል አድርጎ ለሀገር መከታ መሆኑን ለማስመስከር የሚያስችል ወታደራዊ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ዝግጅቱን አጠናክሮ እንደሚገኝም ምክትል አዛዡ ገልፀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.