Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከተማ አስተዳደሮች የ2014 የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከተማ አስተዳደሮች የ2014 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በጅግጅጋ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የክልሉ ከተማ አስተዳደሮች የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ዑመር የተመራ ሲሆን የከተማ አስተዳደሮች የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡

በዛሬው ውሎም የቀብሪደሀርና ቶጎ – ውጫሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የተለያዩ ምክረ ሃሳቦች ተሰጥተዋል፡፡

ግምገማው በክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ዞን መስተዳድሮች የ2014 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ላይ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.