Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሪፓርት ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሪፓርት አፀደቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሁለተኛ ቀን የጉባዔ ውሎው ፥ በትናንትናው ዕለት የከተማ አስተዳደሩ የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቦ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና የምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ በጠየቁባቸው ጉዳዮች ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና አስፍፃሚ አካላት ዝርዘር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ሪፓርቱን ተቀብሎ ማጽደቁን ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.