Fana: At a Speed of Life!

በኮንሶ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ግምቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንሶ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ግምቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ የደቡብ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ከክልሉ ሴቶች አደረጃጀት ጋር በመተባበር አደረገ፡፡

ድጋፉ ለተፈናቃይ ወገኖች እና ለተጎዱ ዜጎች እንደሆነም የኮንሶ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ቢታማ አስታውቀዋል።

የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሪት ኩሪባቸው ታንቱ እንደተናገሩት ፥ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ችግሮች ቢከሰቱም በጉዳቱ መጠን ኮንሶ ዞን ቅድሚያ እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ድጋ የመጀመሪያ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ድጋፉም የምግብ ዱቄት፣ ቁሳቁሶችና አልባሳት ይገኝበታል፡፡

ለተደረገው ድጋፍ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ አመስግነዋል።

ከችግሩ ስፋት አንፃር እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.