Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በፍርድ አሰጣጥ ሂደት ጥፋተኛ በተባሉ ዳኞች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን ፕሬዚዳንቱ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፍርድ አሰጣጥ ሂደት ጥፋተኛ በተባሉ ዳኞች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንና የዳኞችን አቅም እና ክህሎት ለማሳደግ ስልጠና መሰጠቱ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በሦስተኛ ቀን ውሎው የፍርድ ቤቶችን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል፡፡
የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ ÷በፍርድ ቤቶች በዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በፍርድ አሰጣጥ ሂደት ጥፋተኛ በተባሉ ዳኞች የእርምት እርምጃ መወሰዱን የገለጹት÷የዳኞችን አቅም እና ክህሎት ለማሳደግ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
የሴቶች አመራር ለማሳደግ በልዩ ሁኔታ የአቅም ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንነው የተገለጸው፡፡
ከመደበኛ የፍርድ ቤት ጉዳይ ጐን ለ1276 ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸው ለህጻናት እና ለነፍሰጡሮች ቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉም ተመላክቷል፡፡
ከፍትህ አሰጣጥ ፣እና የተገልጋን ፍላጎት ከማርካት እና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከምክርቤት አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች በፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 10 ሚሊዮን 378 ሺህ ብር ገቢ መደረጉም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
የቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ውይይት ከተካሄደበት በኋላ በሙሉ ድምፅ መጽደቁን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.