Fana: At a Speed of Life!

በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የትራንስፎርመር ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ400 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባው የትራንስፎርመር ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡
በምረቃስነ ስርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የፌዴራል መንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ በጫጫ ከተማ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በዓመት ከ750-1ሺህ አዳዲስ ትራንስፎርመሮችን ለማምረት እና ከ1ሺህ 500-2 ሺህ ትራንፎርመር ሙሉ ጥገና ለመስጠትም እቅድ መያዙ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጪ ምንዛሬን ከማዳን አንፃር ሰፊ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡
በዘቢብ ተክላይ እና ግርማ ነሲቡ
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.