Fana: At a Speed of Life!

ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ሰራዊት ገንብተናል-ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ሰራዊት ገንብተናል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ገለጹ።
የሰሜን ምዕራብ እዝ የምስረታ በዓልን ለመዘከር እና ባለፋት አውደ ውጊያዎች በብቃት ተልዕኮ ለፈፀሙ አባላት እውቅና ለመስጠት ያለመ መርኃ ግብር በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ተከናውኗል።
የሰሜን ምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ አሸባሪዎች በጋራ በመኾን የኢትዮጵያ ኅልውና አደጋ ላይ እንዲወድቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀው ይህ የአሸባሪዎች ህልም ከንቱ እንዲቀር ያደረጉ አካላት ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
በጉና፣ ጋሳይ፣ ደብረ ዘቢጥ እና በሌሎችም ግንባሮች በመፋለም የጠላትን ጎንደር እና ባሕር ዳር የመግባት ህልም ቀርቶ በቅርቡ ያለችው ጨጨሆ እንድትናፍቀው አድርጋቹሃልና ክብር ይገባችኋል ነው ያሉት።
በስልት በአካል ብቃት የመፈፀም አቅሙ የጎለበተ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገንብተናል ያሉት ዋና አዛዡ፤ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ማንም ላይ እጇን ቀስራ አታውቅም ለመደፊትም ይህንን አታደርግም ያሉት ጀኔራሉ፤ መከላከያ ኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣ ሽብርም ሆነ ወረራ የመመከት አቅም እንዳለው ገልፀዋል።
ተልዕኳችን ቀጣይ ነው ተግባራችንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ሲሉም ሰራዊቱ ቀጣይም አኩሪ ጀብዱ መፈፀሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጀብደኞቹም በከፍተኛ የሰራዊቱ መሪዎች እውቅና አግኝተዋል።
የ34ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ያለው አድማሱ፤ 501ኛ ኮር አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በክፋለ ጦሩ ከፍተኛ ጀብዱ ለፈፀሙ አባላት እና መሪዎቻቸው ሽልማት መስጠታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ክፍለ ጦሩ ጠላትን እንክትክቱን በማውጣት ደብረ ታቦርን በመመከት ላበረከቱት ከፍተኛ ተጋድሎ የደብረ ታቦርና አካባቢው ሕዝብ በተወካዮቹ አማካኝነት የአፄ ቴዎድሮስን ስዕል በሽልማትነት አበርክቶላቸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.