Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የወንዶች ማራቶን ፍጻሜ ውድድርን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድርን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ 2 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ ከ 36 ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈው፡፡
አትሌት ሞስነት ገረመው ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድርሩን አጠናቋል፡፡
በውድድሩ አትሌት ሌሊሳ ደሲሳ፣ አትሌት ሞስነት ገረመው፣ አትሌት ሰይፉ ቱራ እና አትሌት ታምራት ቶላ ተሳትፈዋል፡፡
ለቤልጂየም የሮጠውና 3ኛ ሆኖ የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኘውም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው በሽር አብዲ ነው።
ካናዳዊው አትሌት ካሜሮን ሌቪንስ 4ኛ ሲወጣ፥ ኬንያዊው አትሌት ጂኦፍሬይ ካምወሮር 5ኛ፥ ኢትጵያዊው አትሌት ሰይፉ ቱራ ደግሞ 6ኛ ወጥተዋል።
አንደኛ ከመውጣቱ ባለፈ ሪከርድ በመስበር አሸናፊ የሆነው ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ከሚያጠልቀው የወርቅ ሜዳሊያ በተጨማሪ፥ 170 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚሸለም ይሆናል። የ100 ሺህ ዶላር ሽልማቱ ሪከርድ በመስበሩ የሚያገኘው መሆኑ ታውቋል።
የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ሞስነት ግረመው ደግሞ 35 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይሸለማል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ሁለት የወርቅና አንድ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመራች ነው። ዛሬ ምሽትና ነገም ተጨማሪ ሜዳሊያዎች እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
በተለይም ዛሬ ምሽት በ10 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃሉ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.