Fana: At a Speed of Life!

ሕዝቡ ካለፈው ዓመት በላቀ ሁኔታ በነቂስ ወጥቶ አረንጓዴ ዐሻራውን እንዲያኖር እና ዳግም ታሪክ እንዲሠራ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ሕዝብ ካለፈው ዓመት በላቀ ሁኔታ በነቂስ ወጥቶ አረንጓዴ ዐሻራው እንዲያኖር እና ሪከርድ በማሻሻል ዳግም ታሪክ እንዲሠራ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በነገው ዕለት በአንድ ጀምበር 400 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅቶችን ጨርሰናልም ነው ያሉት።
ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ኅብረተሰቡ ካለፈው ዓመት በላቀ ሁኔታ በነቂስ ወጥቶ አረንጓዴ ዐሻራው እንዲያኖር እና ሪከርድ በማሻሻል ዳግም ታሪክ እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡
በነገው ዕለት መላው የክልሉ ህዝብ፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በአንድነት ወጥታችሁ አሻራችሁን ለትውልዳችሁ በማሳረፍ የዜግነት ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁም ማለታቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡
የኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 4 ነጥብ 35 ቢሊየን ያህል ችግኞች እንደሚተክሉ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ በክልሉ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከ4 ነጥብ 35 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ነው የታቀደው።
ከዚህ ውስጥ በነገው ዕለት 4 መቶ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር ለመትከል ዝግጅት ተጠኗቋል ነው ያሉት ኃላፊውም።
በክልሉ ለመትከል ከተዘጋጁት ችግኞች 40 በመቶ የደን፣ 10 በመቶ የፍራፍሬ እና ቀሪው ደግሞ የእንሰሳት መኖ መሆኑን ገልጸው፥ በነገው ዕለት የሚተከሉት ችግኞችም ይህን መስፈርት ያሟሉ ናቸው ብልዋል።
በክልሉ 20 ዞኖች እና 19 ከተሞች የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላው መርሐ ግብር እንደሚካሄድ የተናገሩት አቶ አበራ፥ በአሁኑ ወቅትም ችግኞቹ ወደሚተከሉበት ቦታ ተጓጉው ለተከላ ዝግጁ ሆነዋል ነው ያሉት።
ለተከላ ዝግጁ የሆኑት ችግኞች በመንግስት፥ በህብረተሰቡ እና በማህበራት የተዘጋጁ መሆናቸውን ያነሱት ኃላፊው፥ በነገው ዕለት በሚደረጋው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ የማኖር መርሐ ግብር የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል።
ባለፉርት 3 ዓመታት በክልሉ ህብረተሰቡ በችግኝ ተካላ ያደረገው ተሳትፎ በገንዘብ ሲተመን 9 ቢሊዮን ብር እንደሆነም ነው አቶ አበራ ወርቁ የተናገሩት።
በነገው ዕለት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ የማኖር መርሐ ግብር በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች ችግኝ በሚተከልባቸው አካባቢዎች በመገኘት የተለመደውን ሙያዊ እገዛ ያደረጋሉ ብለዋል የቢሮ ኃላፊው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.