Fana: At a Speed of Life!

በታንዛኒያ እስር ላይ የነበሩ 126 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ እስር ላይ የነበሩ 126 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
 
ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ሕገ ወጥ ጉዞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በታንዛኒያ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እየዋሉ ለእስር እንደሚዳረጉ ይታወቃል።
 
ከነዚህም መካከል በሁለተኛው 126 ኢትዮጵያውያን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲበአገሪቱ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመቀናጀት ወደ ኢትዮጵያ መሸኘታቸውተገልጿል፡፡
 
የተቀሩትም በቀጣይ በተቀመጠላቸው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ወደ አገራቸው መመለስ እንዲችሉ እየተሰራ እንደሚገኝ ኤምባሲው አስታውቋል፡፡
 
በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ የሚያደርጉ ሲሆን÷በመንገዳቸው ላይም ለረሃብ፣ ለእስር፣ ለአስከፊ ስቃይ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.