Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በአንድ ጀምበር 400 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ በክልሉ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የዘንድሮውን ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ አስጀምረዋል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በክልሉ በሚገኙ 20 ዞኖች እና 19 ከተሞች እንደሚከናወንም ነው የተገለጸው፡፡

በሎሚ ወረዳ እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ÷ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 300 ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ዞን ብቻ ከ25 ሚሊየን በላይ ችግኝ በዛሬው ዕለት እንደሚተከል በመርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ውስጥ የኤክስፖርት ደረጃ ያላቸው አቮካዶዎችን ጨምሮ 125 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞችም የሚተከሉ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ ለመትከል ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ የደን፣ 10 በመቶው ፍራፍሬ እና ቀሪው ደግሞ የእንስሳት መኖ ችግኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በይስማው አደራው

 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.