Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የ2014 ዓ.ም ወጣቶች ክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር አገልግሎት ዛሬ ተጀምሯል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ መርሐ ግብሩን በአለታ ወንዶ ከተማ በአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት በማስጀመር በይፋ ከፍተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተገኝተዋል።

በክልሉ በዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር በክልሉ ከ567 ሺህ በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከመርሐ ግብሩ በተጨማሪ በአለታ ወንዶ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.