Fana: At a Speed of Life!

የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድሮችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጋራ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የሁለቱን ክልሎች ለማስተሳሰር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶር ይልቃል ከፋለ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰንን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል የስራ ሐላፊዎች በተገኙበት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በሆነ ከርበር በተባለ ቦታ መርሐ ግብሩ መካሄዱ ተገልጿል፡፡
መርሐ ግብሩ ”ጥላቻን ነቅለን ወንድማማችነትን እንትከል” በሚል የወንድማማችነት ፓርክ ውስጥ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.