Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ተሰርዘዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በርካታ አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን ቀውስ ለመቋቋም በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎቻቸውን መሰረዛቸው ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በርካታ አየር መንገዶች ከጣሊያን ወደ ተለያዩ ሃገራት እና ወደ ጣሊያን የሚያደርጓቸውን በረራዎች እየሰረዙ ነው።

በጣሊያን የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የጉዞ እገዳ መጣሏ ይታወሳል።

የአየርላንዱ ሪያንኤር ወደ ጣሊያን የሚያደርገውን ጉዞም ሆነ ከጣሊያን ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚደረግን ጉዞ እስከተያዘው ወር መጨረሻ ድረስ ሰርዟል።

ከዚህ ባለፈም በርካታ አየር መንገዶች ወደ ጣሊያን የሚያደርጓቸውን በረራዎች መቀነሳቸውን ገልጸዋል።

የኖርዌዩ አየር መንገድም በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ከሚያደርገው በረራ ውስጥ 15 በመቶውን እንደሚያቋርጥ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም በጊዜያዊነት የሰው ሀይሉን ለመቀነስ ማቀዱም ነው የተነገረው።

የአሜሪካ አየር መንገድ ከሀገር ውስጥ በረራዎቹ ውስጥ 7 ነጥብ 5 በመቶ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.