Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በደሴ ከተማ ጦሳ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በማካሄድ ላይ ነው።
በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በክልሉ የሚገኙ የአሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና የደሴ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች መሳተፋቸው ታውቋል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ በየዓመቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እንደሚያካሂዱ የተገለጸ ሲሆን ፥ በዛሬው ዕለት በጦሳ ተራራ ላይ 3 ሺህ 200 ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.