Fana: At a Speed of Life!

በጋና ገዳይ የማርበርግ ቫይረስ መከሰቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋና በተላላፊነቱ እና በገዳይነቱ ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የሚነገርለት የማርበርግ ቫይረስ መከሰቱን ገለጸች፡፡

በጋና ደቡብ አሻንቲ ግዛት ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ከተጠቁ በኋላ ሆስፒታል ደርሰው ሕይወታቸው እንዳለፈም ነው የተመላከተው፡፡

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የጤና ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ÷ ከታማሚዎቹ ጋር ንክኪ ነበራቸው ያሏቸውን 98 ያህል ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረጉላቸው ነው፡፡

ቫይረሱ በመጀመሪያ ከሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች የሚተላለፍ ሲሆን ቀጥሎም ከሰዎች ወደ ሰዎች ከሰውነታቸው በሚወጣ ፈሳሽ እና ንክኪ አማካኝነት በቀላሉ ሊተላለፍ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የጡንቻ ሕመም፣ ደም ማስመለስ እና የሰውነት መድማት የሕመሙ ምልክቶች እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡

ማርበርግ እስካሁን ምንም ዓይነት ሣይንሳዊ ሕክምና እንዳልተገኘለትና ውሃ አብዝቶ መጠጣት እና የሚታዩ የሕመም ምልክቶችን ያማከለ ሕክምና መስጠት የሕመምተኛውን የመዳን ዕድል እንደሚያሻሽል ቢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.