Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ በአለታ ወንዶ ከተማ የተሰሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በአለታ ወንዶ ከተማ የተሰሩ የመንገድ መሰረተ ልማዶችን ጎብኝተዋል።
የክልሉ ሕዝብ በግንባር ቀደምትነት የልማት ጥያቄ ከሚያነሳቸው ጉዳዮች መካከል የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ ከሲዳማ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ፣ የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ
አብርሃም ማርሻሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ተዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.