Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮቹን እየመረጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫ እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 2ኛ ዙር ሀገር አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባኤው ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫም እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 261ዱ መገኘታቸው ታውቋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ እንዳልተገኙ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 1ኛ ዙር ሀገር አቀፍ ጉባኤ ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.