Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ÷ 1ሺህ 40 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት መሄዳቸውም ተመላክቷል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 52 ሺህ 878 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.