Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በ2015 ዓ.ም በጀት ያልተማከለ አስተዳደር ስርዓት ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ245ኛ መደበኛ ስብሰባው በ2015 ዓ.ም በጀት ያልተማከለ አስተዳደር ስርዓት ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።
 
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከፌደራል መንግስት ለ2015 በጀት ዓመት የተመደበለትን ጥቅል የድጎማ በጀት ለዞኖች እና ለልዩ ወረዳዎች የሚከፋፈልበት መንገድ ግልጸኝነትን እና ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ መሆን እንደሚገባው መክሯል።
 
የ2015 በጀት ዓመት የሃብት ክፍፍል መነሻ ያደረገው የወጪ ፍላጎት ማመጣጠኛ ቀመርን ሲሆን÷ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት፣ የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች አስተዳደር መረጃዎች፣ የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች መረጃዎች፣ ዘመናዊ የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሁም ተያያዥ የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ እንደሆነም መስተዳድር ምክር ቤቱ በዝርዝር መክሮበታል።
 
ቀመርን መሰረት ያደረገው በጀት ለዞኖች እና ለልዩ ወረዳዎች እንዲወርድ ማድረግ ያለውን ውስን ሀብት በፍትሃዊነት ለማከፋፈል ከማገዙም በላይ የህዝቦችን አንድነት እና መተማመንን ይበልጥ እንደሚያጎለብት መስተዳድር ምክር ቤቱ በስፋት መክሮበታል።
 
የሃብት ክፍፍል ስርዓቱ የፌዴራል መንግስት የተከተለውን ሂደት መሠረት ያደረገ ሲሆን÷ የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ተሳትፎ አስፈላጊነት ታምኖበት የሚመለከታቸው የታችኛው መዋቅር አካላት ተገኝተው ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሰጡበት መስተዳድር ምክር ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.