Fana: At a Speed of Life!

የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ለልማት ሥራው እንቅፋት እንዳይሆን እንሠራለን – ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ለልማት ሥራው እንቅፋት እንዳይሆን በልዩ ትኩረት እንሠራለን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመስገን ጥሩነህ፣ ሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ባለሃብቶች በትጋት በመሥራት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

በአንድ እጃችን ሰላምና ፀጥታችን በሌላ እጃችን ደግሞ ልማታችንን እያከናወን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ባለሀብቶች እያለሙት ያለው ልማት ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል፡፡

ሰላማችንን እየጠበቅን ከሄድን ከዚህ የበለጠ እናመርታለን ያሉት ዶክተር ይልቃ÷ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ለልማት ሥራው እንቅፋት እንዳይሆን እንሠራለን ብለዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለመፍታት ምርትና ምርታማነትን መጨመር አለብንም ብለዋል።

ባለሃብቶቹ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠሩ መሆኑን ገልጸው÷ ባለሃብቶች በልማት ሥራዎቻቸው ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የሥራ እድል መፍጠራቸውን አብራርተዋል፡፡

ግብርናውን ከኢንዱስትሪው ጋር እያመጋገቡ እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመው÷ መንግሥት በቂ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን እየለየ ቢሰጠን የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀር ሥራ መሥራት እንችላለንም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.