Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ 3ኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች።
ከሰአት በኋላ በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቃለች።
ርቀቱን 2 ሰአት ከ18 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው።
በዚህም የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች።
ኢትዮጵያም 3ኛውን የወርቅ ሜዳልያ በሻምፒዮናው አግኝታለች።
በውድድሩ የኬንያ እና የእስራኤል አትሌቶች 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.