Fana: At a Speed of Life!

በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የመኸር እርሻ ከተጀመረ ወዲህ እስካሁን 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆልቲ ካልቸር ዘርፍ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ መለሰ መኮንን የመኸር እርሻ እንቅስቃሴን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በተያዘው የመኸር እርሻ 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬትን በዘር ለመሸፈን ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ ውስጥም 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬትን በክላስተር በማረስ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የመኸር እርሻው ከተጀመረ እስከ አሁን ድረስ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑንም ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት እንደ ሀገር በዘር ከሚሸፈነው መሬት 400 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ እንቅስቃሴ መገባቱን ጠቁመዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.