Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ዕዝ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጣን አደጋ በአስተማማኝ ሁኔታ መመከት የሚያስችል አቅም ገንብቷል – ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጣን አደጋ በአስተማማኝ ሁኔታ መመከት እና ማሸነፍ የሚያስችል አቅም መገንባቱን የዕዙ ዋና አዛዥና የአድዋ ሜዳይ ተሸላሚ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት ገለጹ፡፡

ሌተናል ጀኔራል መሰለ ከምዕራብ ዕዝ የግዳጅ አፈፃፀምና የቀጣይ ዝግጁነት ጋር በተያያዘ ከዕዙ ጠቅላይ መምሪያ መኮንኖች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ጥሎት የነበረውን የሰራዊት ስነ ልቦና የማድረግ አቅምና ኢትዮጵያዊ ስሜት በአጭር ጊዜ በመገንባት፣ የውጊያ ስነ ምግባርን በማረጋገጥ የማይተኛ ቆራጥ፣ ጀግናና አሸናፊ ሠራዊት መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ የነበረውን የወታደራዊም ይሁን የፖለቲካዊ የበላይነት በህዝብ ጥረትና ግፊት ካጣ በኋላ እኔ እንደፈለግሁ ያላደረግኋት ሀገር መፍረስ አለባት በማለት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ሳይቀር ጥምረት በመፍጠር ያልሞከረው ያልተመኘው ጥፋት የለም ያሉት ሌ/ጀኔራል መሰለ፥ እስከ መስዋዕትነት በዘለቀው ተጋድሏችን ግን ኢትዮጵያን ማዳን ችለናል ብለዋል።

ዕዙ የጠላትን አቅምና አሰላለፍ ቀድሞ በማወቅ የውጊያ ዝግጁነቱን እንዳረጋገጠ መግለጻቸውንም ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን የተደራጀ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ጦርነት ያሸነፍነው ፍትሃዊ ስለነበርን ነው ሲሉም የዕዙ ዋና አዛዥ ተናግረዋል።

ዕዙ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጣን የቱንም አደጋ በአስተማማኝ ሁኔታ መመከትና ማሸነፍ የሚችል አቅም መገንባቱንም የዕዙ ዋና አዛዥ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.