Fana: At a Speed of Life!

ገቢዎች ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ከ336 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የበጀት ዓመት ከ336 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዚህ በጀት ዓመት ሊሰበስብ ካቀደው 360 ቢሊየን ብር፥ 336 ቢሊየን 710 ሚሊየን 021ሺ 930 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 93 ነጥብ 53 በመቶ ማሳካቱ ተገልጿል፡፡

አፈጻፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 57ቢሊየን 494 ሚሊየን 923 ሺህ 697 ወይም የ20 ነጥብ 59 በመቶ እድገት እንዳለው ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ምንጭ የአገር ውስጥ ታክስ 196 ቢሊየን 211 ሚሊየን 638 ሺህ 548 ብር የሚሸፍን ሲሆን፥ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 140 ቢሊየን 498 ሚሊየን 338ሺ 382 ብር መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ሚኒስትሩ የገቢ አፈጻጸሙ ከፍ እንዲል ላደረጉ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለግብር ከፋዮች እንዲሁም ለአጋር አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.