Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ከግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች ጋር በመዲናዋ ስላለው የፀጥታ ሁኔታ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የመጡ ኤጀንሲዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመዲናዋ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የሚደራጁ ኤጀንሲዎችን ጨምሮ 223 ኤጀንሲዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በሥነ ምግባር የታነፁ ሠራተኞች ያሏቸው ኤጀንሲዎች እንዳሉ ሆነው÷ ለወንጀል የሚተባበሩ ሠራተኞች ያሏቸው ኤጀንሲዎች አሉ መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላም እና ፀጥታን በማስጠበቅ ሂደት የኤጀንሲዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ኤጀንሲዎች በአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ማስጠበቅ ላይ እና በሥነ ምግባር የታነፁ ሠራተኞችን ማፍራት ላይ እንዴት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው በሚል እና እየታዩ ያሉ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ነው ውይይቱ እየተካሄደ ያለው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.