Fana: At a Speed of Life!

ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት ፍትሃዊ የበጀት አጠቃቀም ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዜጎች ልማት እና ለአጠቃላይ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት በጀትን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡

በደቡብ ክልል በ2015 በጀት ዓመት የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ርስቱ ይርዳ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ የፌደራል መንግስት ለክልሎች የሚመድበውን በጀት ለዜጎች ብዝሀነትን ባማከለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ የክልሎች ኃላፊነት ነው ፡፡

በሕዝቦች መካከል መተማመን፣ መተባበር እንዲሁም ወንድማማችነትን ለማስረጽ ሀብትን በፍትሃዊነት ማከፋፈል ወሳኝ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ÷ በክልሉ ዞን እና ልዩ ወረዳዎች የሚሰበስቡትን ገቢ ለራሳቸው እንዲያውሉ ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር መዘርጋት መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡

በውይይት መድረኩ የክልል፣የዞን እና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.