Fana: At a Speed of Life!

የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በ100 ወረዳዎችና በ28 ክላስተሮች እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በ100 ወረዳዎችና በ28 ክላስተሮች እየተተገበረ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በሚኒስቴሩ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በአዳማ  ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እንደገለጹት÷በቆላማ አካባቢዎች ያለውን ፀጋ በመጠቀም የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንድርያስ ጌታ በበኩላቸው÷መሠረታዊ የኑሮ ለውጥ ለማምጣት የአርብቶ አደሩን ሕይወት ማሻሻል ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ በ2015 ውኃን መሠረት አድርጎ የሚሰሩ ሥራዎችን አቅደን እንሰራለን ብለዋል፡፡

የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በ100 ወረዳዎች እና በ28 ክላስተሮች እየተተገበረ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ሰዒድ ዑመር ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች እየተተገበረ ሲሆን÷ በቀጣይም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንደሚተገበር መገለጹን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.