Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በሕንድ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በህንድ ኒውደልሂ ተካሄደ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የሕንድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አኑፕሪያ ፓተል ናቸው ውይይቱን ዛሬ ያካሄዱት፡፡

የሕንድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አኑፕሪያ ፓተል ባደረጉት ንግግር፥ ከአቶ መላኩ አለበል ጋር ያደረጉት ውይይት “የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ጠንካራና ጥልቅ ለማድረግ የሚያችል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ መላኩ አለበል በ17ኛው የኤግዚም ባንክ እና የአፍሪካ ዕድገት አጋርነት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ኒውደልሂ መግባታቸውን በሕንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.