Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ልማትን ማደስ የሚቻለው በቂ እውቀት ያላቸው መምህራንን መፍጠር ሲቻል ነው – አቶ ደስታ ለዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ልማትን ማደስ የሚቻለው በቂ እዉቀት ያላቸው መምህራንን መፍጠር ሲቻል ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ለዳሞ ገለጹ።

ርዕስ መስተዳድሩ ይህን ያሉት የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ”የሲዳማ ትምህርት ተሃድሶ” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።

ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር ትምህርት ትልቅ ሚና ስላለው ለስኬቱም የመንግስት በጀት ብቻ በቂ ስለማይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የሲዳማ ክልል በሀገር ደረጃ ያለውን የትምህርት ጥራት መስፈርት እንዲያሟላ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለተማሪዎች ማድረስ ይጠበቃል ብለዋል።

ለዚህም ዕውቀት ያላቸው መምህራንን መፍጠር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው ፥ ላለፉት አራት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ቢሆንም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አልተቻለም ብለዋል።

ይህንን ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸውም ፥ በክልሉ 2 ሺህ 246 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ገልጸው፥ በአገር ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎች ጥቂት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በደብሪቱ በዛብህ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.