Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከፍተኛ መጠን ያለው የጋዝ ምርት ወደ ቻይና ላከች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሳይቤሪያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር አማካኝነት በየቀኑ ከፍተኛ መጠን ያለው ጋዝ ለቻይና ማቅረቧ ተገለፀ።

የሩሲያው ጋዝፕሮም ኩባንያ አቅርቦቱ ከቻይናው ሲ ኤን ፒ ሲ ኩባንያ ጋር ባደረገው የረጅም ጊዜ ውል መሰረት የተፈፀመ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ቻይና የተላከው የጋዝ ምርት መጠን ከ60 በመቶ በላይ አድጓል።

የሳይቤሪያ የኃይል መስመር ከሳይቤሪያ ወደ ቻይና የተዘረጋው የምስራቃዊ የጋዝ መስመር አካል ሲሆን፤ የሩስያ ጋዝ ዋና ሸማች የሆነችው ቻይናም በመስመሩ በኩል የተፈጥሮ ጋዝን ከሀገሪቱ ታስገባለች።

ወደ ቻይና የሚላከው ጋዝ ጭማሪ ያሳየው ባለፈው ወር በኖርድ ስትሪም ወደ አውሮፓ የተዘረጋው አንድ የጋዝ መስመር መቋረጡን ተከትሎ ነው።

ጋዝፕሮም በሩሲያ ላይ የተጣለውን ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ለመስመሩ ቴክኒክ ችግር ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

ሞስኮ አስተማማኝ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ እንደሆነች እና ለደንበኞቿም የውል ግዴታዎችን እንደምትወጣ ደጋግማ እየተናገረች ትገኛለች- አርቲ በዘገባው እንዳሰፈረው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.