Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ46ሺህ በላይ ዶላርና የወርቅ ጌጣጌጦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ46ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላርና የተለያዩ ይዘት ያላቸው የወርቅ ጌጣጌጦች መያዙን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት ፥ ገንዘቡ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በሚጓዘው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሽከርካሪ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ነው የተያዘው።

ፖሊስ ባደረገው ድንገተሻ ፍተሻ በከተማዋ ደምበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ልዩ ቦታ ቢኤም ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ትናንት ምሽት 4 ፡30 ላይ መያዙን ተናግረዋል።

በዚህም 46 ሺህ 421 የአሜሪካን ዶላርና የተለያየ ይዘት ያላቸው 16 የአንገት ሃብሎች፣ የእጅና የጆሮ ጌጣጌጦች መያዛቸውን አመልክተዋል።

አሽከርካሪውን ጨምሮ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.