Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ቴህራን ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢራን ቴህራን ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን በቴህራን ቆታቸው ከኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ከቱርክ አቻቸው ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

መሪዎቹ በሶሪያ ጉዳይ ላይ በዋናነት ሊመክሩ እንደሚችሉ አር ቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርኩ አቻቸው ጋር በኢራን መዲና ቴህራን ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት፥ የዩክሬን የእህል ምርቶችን በጥቁር ባህር ወደብ በኩል ወደ ውጭ መላክን አስመልክቶ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ የተሟላ ስምምነት ላይ ገና ለመድረስ አልተቻለም።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በዚሁ ወቅት የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ላደረጉት የሽምግልና ጥረት እንዲሁም የምግብ ዋስትና ችግሮችን ለመፍታትና የምግብ እህልን በጥቁርር ባህር በኩል ወደ ውጭ ለመላክ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር መድረክ እንዲዘጋጅ በማድረጋቸው አመስግነዋቸዋል ሲል የሩሲያው የዜና አገልግሎት ድርጅት ታስ ዘግቧል።

ሩስያ በዩክሬይን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተችበት ካለፈው የካቲት አጋማሽ ጀምሮ በተፈጠረውና እየተባባሰ በመጣው የምግብ እህልና ምግብ ነክ ችግሮች ምክንያት፥ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ላይ በዘርፉ ባለሙያዎች አገላለጽ “ የእህል ቀውስ “ መከሰቱ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.