Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኀብረት በሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለማለዘብ ማቀዱ ተነገረ 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኀብረት በሞስኮ ላይ የጣለውን ማዕቀብ በማሻሻል በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀውስ ውስጥ ያለውን የምግብ እና የማዳበሪያ ንግድ ለማቀላጠፍ ማቀዱ ተነገረ።

የሚደረጉት ለውጦች የአውሮፓ ኀብረት አባል ሀገራት በሩሲያ ከፍተኛ ባንኮች ላይ የጣሉባቸው ማዕቀብ እንዲነሳ እና በማዕቀቡ ምክንያት  በዓለም አቀፉ የምግብና የማዳበሪያ ንግድ ላይ የተፈጠረውን ማነቆ ለማላላት ያስችላል ተብሏል።

ማሻሻያዎቹ በመጪው ረቡዕ ይፀድቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በተለይም የሩስያ ባንኮች እና ሌሎች  አበዳሪ ተቋማትን እንደሚመለከት አየሁት ያለውን ረቂቅ ሰነድ ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

ማሻሻያዎቹ የሚጸድቁትም ስንዴና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብርና እና የምግብ ምርቶችና ግብአቶችን ለመግዛት፥ ወደ ውጭ ለመላክ ወይም  ለማጓጓዝ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ነጋዴዎች ወደ ውጭ የሚልኳቸውን የምግብ አቅርቦቶች አቋርጠው የነበሩ  ቢሆንም፥ ከሩሲያ ወደቦች የሚላከውን ምግብ ለማቀላጠፍ የሚረዳ እንደሚሆንም በዘገባው ተጠቅሷል።

ሩሲያ በዓለም ላይ ትልቋ  ማዳበሪያ እና ስንዴ ላኪ ሀገር መሆኗን ያስታወሰው ዘገባው፥ ማሻሻያው የሚማዕቀቡ በወሳኝ የሸቀጦች ንግድ ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ተፅዕኖና የአፍሪካ መሪዎችን ትችት ተከትሎ ነው ብሏል።

በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ግጭት እና በሩሲያ ላይ የተጣለው ሰፊ እገዳ የምግብ አቅርቦት እጥረት፣ የእህል እና የማዳበሪያ ዋጋ መጨመር እና የዓለም የምግብ ቀውስ ስጋትን አስከትሏል ሲል አርቲ ሮይተርስን ጠቅሶ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.