Fana: At a Speed of Life!

በታንዛንያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛንያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 66 ኢትዮጵያውያን በፈቃዳቸው በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የታንዛንያ ዳይሬክተር ዶክተር ቃሲም ሱፊ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ለዜጎቹ መመለስ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት፣ በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና የታንዛንያ የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ላደረጉት ትብብር እንዲሁም የስዊድን መንግሥት ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ÷ በአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከ12 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ ከሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይከናወናል ማለታቸውን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.