Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔዎች በማሳለፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
የጉባኤው አፈ ጉባኤ አቶ ሙህይዲን አህመድ ጉባዔው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ጠቁመው÷ በዚህም የጉባዔው የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መገምገሙን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ የተሟላ አደረጃጀት ኖሮት የተቋቋመለትን ዓላማ ከማሳካት አንፃር የነበሩ ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ስለመሆናቸው መገምገሙን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም እና ትምህርት ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን መገምገሙን ገልጸው÷ በዚህም ጉባዔው አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገምግሟል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በጉባዔው የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድና የጉባዔውን የአራት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መርምሮና አቅጣጫ በማስቀመጥ አጽድቋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ የብሔረሰቡን ባህል፣ ቋንቋና ቅርስ ከመጠበቅ እና ከማልማት አንፃር በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡
ጉባዔው የባህል፣ የታሪክ እና ቅርስ እንዲሁም የትምህርትና የቋንቋ ቋሚ ኮሚቴ ያሉት ሲሆን÷ በጉባዔው የሁለቱም ቋሚ ኮሜቴ ሰብሳቢ፣ ጸሐፊ እና አባላት ተመርጧል ብለዋል፡፡
የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ በሕገ መንግሥት በተሰጠው ስልጣን መሰረት÷ የሐረሪ ሕዝብን ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋና ቅርስ የመጠበቅና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ ተግባራትን የመከታተል እንዲሁም ሕግ የማውጣትና ተግባራዊ የማድረግ ሥራ ያከናውናል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.