Fana: At a Speed of Life!

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 200 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል የተባለ የስራ ሀላፊ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ 200 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል ተገኝቷል የተባለ የቤቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ ገለፀ፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ባህሩ ተክሌ እንዳስታወቁት÷ ግለሰቡ ሀላፊነቱን በመጠቀም ሰነድ አልባ የሆነን መኖሪያ ቤት ሕጋዊ ካርታ እሰጣለሁ በሚል የማጭበርበር ቃል ከአንዲት ግለሰብ አትላስ አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ሱቅ በር ላይ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ ነው።

ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ግለሰቦችን ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን ገልፀው÷ አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሚሞክሩ ሌሎች ግለሰቦችም ከዚህ በመማር ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ሕብረተሰቡም ድርጊቱን በማጋለጥ ሂደት ላደረገው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

ሕብረተሰቡ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችን ሲያገኝ በአፋጣኝ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ዋና ኢንስፔክተሩ  ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.