Fana: At a Speed of Life!

 በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ 21 የታጠቁ የሽፍታ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 21 የታጠቁ የሽፍታ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡

የቡድኑ አባላት በቀጠናው እየተካሄደ ካለው ሕግ ማስከበር ተግባር ጋር ተያይዞ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ዛሬ ለወረዳው ኮማንድ ፖስት በሰላም እጅ መስጠታቸውንና ትጥቃቸውን ማስረከባቸውን የመተከል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ  የሽፍታው ቡድን አባላት እንደገለጹት÷ የተሳሳተ የፖለቲካ አጀንዳዎችን ተቀብለው  ጫካ ውስጥ በመንቀሳቀስ ሲያካሂዱት የነበረው ሕገ ወጥ ተግባር ተቀባይነት የለውም፡፡

በመሆኑም በዚህ  እኩይ ተግባር ውስጥ የሚገኙ የሽፍታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

እጃቸውን  በሰላማዊ መንገድ ለመንግሥት እጅ የሰጡ አካላትም ታጥቀውት የነበረውን÷ ክላሽ 1፣ አጭር ምንሽር 5፣ ቤልጅግ 5፣ አብራራው 2፣  ምንሽር 3፣ ጅምስሪ 1፣ እሰኬስ 3 እና ኤም ዋን 1 አስረክበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.