Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ ለደኅንነቴ ሥጋት ሆኗል ስትል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ በታይዋን አቅራቢያ መታየቱን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ሰጠች፡፡

ቻይና “አሜሪካ ሠላሜን ለማወክ እና በቀጠናው አለመረጋጋትን ለመፍጠር በሚሳኤል ተሸካሚ የባሕር መርከብ የታገዘ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አድርጋለች” ስትል ገልጻለች፡፡

አሜሪካ በበኩሏ በነጻ ባሕር ላይ የማደርገው ቅኝት አካል እና ዓለም አቀፍ ኅግን ተከትየ የምፈጽመው ነው ብላለች።

አሜሪካ ቻይናን እልህ ውስጥ ለማስገባት መሰል ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎችን በደቡብ ቻይና ባሕር አካባቢ ስታደርግ መቆየቷንና ከቻይና በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ቻይና በታይዋን የሚገኙት ደሴቶች ግዛቶቼ ናቸው ስትል መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን የአሜሪካ ትንኮሳም ለታይዋን ነጻ አውጭዎች ያላትን ድጋፍ ለማሳየት ሆን ብላ የምታደርገው ነው ስትል ትወቅሳለች።

ቻይና ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነቷን ላለማስደፈር ጦሯ ዘወትር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ሺ ዪ የተባሉ ኮሎኔል መናገራቸውን ሲ ጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.