Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃን ለማጋራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረራሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂ አማካኝነት መረጃን ለማጋራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረራሙ፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው÷ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ነው፡፡
ዶክተር ለገሰ ቱሉ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ዘመኑ የሚፈልገውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ ለመሥራት መረጃን በተቀላጠፈ እና በተሻለ ትንተና ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰው ሰራሽ አስተውህሎ መታገዙ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ይህን ለማሳካትም ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር ለመስራት ስምምነት መደረሱን ጠቅሰዋል።
ስምምነቱ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ እገዛ ሲሆን÷ አጠቃላይ በዚህ ዓመት አምስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቼና በበኩላቸው÷ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሕዝብ ተደራሽ የሚያደርጋቸውን መረጃዎች በተቀላጠፈና በተተነተነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ድጋፍ ያእንደሚያደርግ ገልጸዋል።
መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም በመተንተን እና ተደራሽ በማድረግ በቴክኖሎጂ ለማገዝ ተቋሙ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.