Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል የ2014 ዓ.ም አፈፃፀምን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የ2014 ዓ.ም አፈፃፀምን ከክልል፣ ከከተማ እና ከወረዳ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ጋር እየገመገሙ ነው፡፡

በግምገማው ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የክልል፣ የከተማና የወረዳ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የ2014 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት በስራ ኃላፊዎች እየቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ ምላሽ እየተሰጠበት መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.