Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተጀመረው የ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክት በልደታ ክፍለ ከተማ ጌጃ ሰፈር የምገባ ማእከል ፣ የመኖሪያ ቤቶች ፣ ሱቆች፣ የዳቦ መሸጫና የከተማ ግብርና ስራ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ለባለቤቶቹ አስረክበዋል፡፡

ግንቦት 12፣ 2014 ዓ/ም የተጀመሩት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶቹ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በዳሽን ባንክ አማካኝነት የተገነቡት እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

የምገባ ማዕከሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለይ ለሚገኙ 3ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች ጤናው የተጠበቀ ምግብ እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው የተባለ ሲሆን ፥ ከዚህ ቀደም በከተማ አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙት ጋር በጠቅላላው ሰባተኛው የምገባ ማዕከል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግንባታው በአጠቃላይ 40 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተገልፆ የምገባ ማዕከሉን 21ሚሊየን ብር የሚሆነውን የአንድ ዓመት የምገባ ወጪውን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በዳሽን ባንክ በመተባበር እንደሚሸፍኑትም ነው የታወቀው፡፡

በፕሮጀክቱ የተፈናቀሉ ሰዎች የቀደመ ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል 23 ሱቆች፣ ሥምንት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም ለምገባ አገልግሎት የሚውል የጋሮ አትክልት ግንባታም ተከናውናል፡፡

በማህሌት ተ/ብርሃን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.