Fana: At a Speed of Life!

በበጀት አመቱ 17 ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በራስ አቅም 17 ፕሮጀክቶች ገንብቶ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
ተቋሙ እንዳስታወቀው÷ ከተጠናቀቁት ፕሮጀክቶች መካከል ሁለቱ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ቢሮ፣ 11 የሲቪል ሥራዎች ግንባታ ቢሮ አራቱ ደግሞ የሲቪል ሥራዎች ጥገና ቢሮ ናቸው፡፡
በዚህም በመምሪያው በመከናወን ላይ ከሚገኙት 37 የተለያዩ ፕሮጀክቶች መካከል 20 ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ 17 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውና የተቀሩት ሦስት ፕሮጀክቶች ግን በሲሚንቶ አቅርቦት ችግርና በማሽነሪ ብልሽት ምክንያት በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት አለመጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡
በመምሪያው ከሚከናወኑት ፕሮጀክቶች መካከል አስሩን በ2015 በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪ ም÷በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከጦርነት ነፃ በወጡ አካባቢዎች የወደሙትን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የጥገና ስራ እና የደብረ ዘይት አየር ኃይል ግቢ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የማስዋብ ስራ መከናወኑ ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መምሪያው ባከናወናቸው ስራዎች 5 ነጥብ 25 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማዳን መቻሉን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.