Fana: At a Speed of Life!

አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች ሰቆጣ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አስቸኳይ የሰብዓዊ የምግብ እርዳታ የጫኑ 13 የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች ሰቆጣ ከተማ ገብተዋል፡፡
 
የሰብዓዊ እርዳታው በኤፍ ኤች ኢትዮጵያ አስተባባሪነትና በዓለም ምግብ ፕሮግራም አቅራቢነት በአበርገሌ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ያሉ አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የወረዳው ተወካይ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ እነተ ተናግረዋል፡፡
 
ተወካይ አስተዳዳሪው በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል ለሁለት ወር የሚሆን 9 ሺህ 285 ነጥብ 9 ኩንታል ስንዴ፣ 928 ነጥብ 59 ኩንታል ክክ እና 3 ሺህ 335 ሊትር ዘይት እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡
 
ከተመደበው 9 ሺህ 285 ነጥብ 9 ኩንታል ስንዴ ውስጥ 2ሺህ 991 ነጥብ 5 ኩንታል ስንዴ ሰቆጣ መግባቱን እና ቀሪው 6 ሺህ 294 ነጥብ 4 ኩንታል ስንዴ በቅርቡ ሰቆጣ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
 
ድጋፉን በአበርገሌ ወረዳ ለሚገኙ የዕለት ደራሽ ምግብ ፈላጊዎች ለማሰራጨት ከሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከሰቆጣ ተነስተው ወደ አበርገሌ ወረዳ ኒሯቅ ከተማ እንደሚሄዱ ከሚመለከታቸው የረድኤት ድርጅት ኃላፊዎች ጋር የጋራ ውይይት መደረጉም ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.