Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የስራ አመራር ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ) የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የስራ አመራር ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የፓርቲውን የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡

የዋና ጽህፈት ቤቱ የተለያዩ ዘርፎች ከክልልና ከተማ አስተዳደር የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ዘርፎች ጋር በጋራ የገመገሙትን የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አቅርበዋል፡፡

በስራ አመራር ኮሚቴው ውይይት ወቅት በዓመታዊ አፈጻጸሙ የታዩ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲሁም በ2015 በጀት ዓመት በትኩረት እንዲተገበሩ የተቀመጡ ተግባራት ቀርበዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ÷በእቅድ አፈፃፀም የታዩ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በክፍተት የታዩትን ደግሞ ለማካካስ እንዲቻል በውይይቱ የተነሱ አንኳር ጉዳዮች የ2015 እቅድ አካል ሆነው እንዲካተቱ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.